የCRM+ ስርዓት የስራ ክልል (Scope)
CRM+ ስርዓት የሚከተሉትን ዋና ዋና ነገሮች እና ሂደቶች ይሸፍናል፦
ተጠቃሚዎች እና ሚናዎች
ሠራተኞችን እና አስተዳዳሪዎችን በተለያዩ ሱቆች እና መደብሮች ውስጥ ያስተዳድራል
ሱቆች እና መደብሮች
ከአንድ በላይ ሱቆችን ፡ መደብሮችን እና መጋዘኖችን በቀላሉ ማስተዳደር እና መቆጣጠር
በሱቆች እና በመጋዘኖች የሚገኙ ንብረቶችን አንድ ላይ እና ለየብቻ በመነጣጠል በብር ተምኖ በማስቀመጥ ያለን አቅም ለማወቅ የሚያስችል ነው
ትዕዛዞች እና ሽያጮች
የደንበኞች ትዕዛዞች፣ ሽያጮች እና ክፍያዎች ያስተዳድራል
እቃዎች (Inventory)
የምርት ክምችትን በሱቆች፡በመጋዘኖች እና በመደብሮች መካከል የእቃ ማዛወር ያመቻቻል ፡ይከታተላል
ያለቁ ፡ በማለቅ ላይ የሚገኙትን እና ከአገልግሎት ውጪ የሆኑ ምርቶችን ማሳወቅ
ክሬዲት
የደንበኞች ዕዳ እና የክፍያ ታሪክ ያስቀምጣል
ፋይናንስ
የባንክ ሂሳቦች፣ የጥሬ ገንዘብ ግብይት እና የVAT መጠን ያስቀምጣል
የCRM+ ስርዓት ዓላማ (Objective)
CRM+ ስርዓት ለማሳካት የተፈጠረው የተወሰኑ ግቦች እነዚህ ናቸው፦
የንግድ ሥራዎችን ማመቻቸት
ሽያጭ፣ ትዕዛዝ፣ ክምችት እና ክፍያ በቀላሉ እና በትክክል እንዲከናወኑ ማድረግ
የፋይናንስ ትክክለኛነት ማረጋገጥ
የሚገኙት ገንዘቦች፣ የሚውሉት ዕዳዎች እና የቀረቡት ታክስ በትክክል መመዝገብ
የክሬዲት አስተዳደርን ማሻሻል
የደንበኞች ዕዳ በራስ-ሰር መከታተል እና ጊዜ ያለፈበት ዕዳዎችን ለማወቅ
ሪፖርት ማውጣትን ማስቻል
ከፍተኛ ሽያጭ ያደረጉ መደብሮች እና ምርቶች ለማወቅ ይረዳል
የCRM+ ስርዓት ዓላማ (Purpose)
የCRM+ ስርዓት በአጠቃላይ ዋናው አላማው፦
የንግድ ሥራውን ማዕከላዊ እና አስተማማኝ ማዕከል በመፍጠር ሁሉንም የንግድ ሂደቶች በቀላሉ፣ በትክክል እና በአውቶማቲክ እንዲከናወኑ ማድረግ
የሥራ ብቃት ማሳደግ
የፋይናንስ ቁጥጥር
በመረጃ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ
CRM+ ስርዓትን ለንግድዎ ይጠቀሙ
የንግድ ሂደቶችዎን ለማዘመን እና ለማሻሻል ከእኛ ጋር ይተባበሩ
የስርዓት ማስኬድ ያግኙን